የአምላክ ልጆች ፋውንዴሽን የመሥከረም2014 ዓ.ም የሥራ እንቅስቃሴ።



Categories:

የአምላክ ልጆች ፋውንዴሽን አባላት፣ ወዳጆች፣ ቤተሰብና አጋሮች በሙሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም ደሰሳችሁ፣ ዓመቱም ለሁላችሁ በሁሉ አቅጣጫ የተሳከ እንዳሆንላችሁ እንመኛለን ።

ፋውንዴሽኑ በእግዚአብሔር ዕርዳታና በእናንተ በጎ ፈቃድ ድጋፍ እንዲሁም በትጋት በሚሠሩ ሠራተኞችና የኮሚቴ ዓባላት የተለያዩ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል። በዚህ ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር እናመሰግናለን ፣ እናንተንም ከልብ እናደንቃለን ። በወሩም የተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች እንደሚከተለው እናቀርባለን።

  • በአራስ ቤታችን እስከ አሁን 44 ሴቶችና 52 ልጆቻቸውን ድጋፍ የሰጠ ሲሆን፣ በመስከረም አዲስ የተጨመሩና አገልግሎት ያገኙ 2እናቶችና
    2 ልጆቻቸው ሲሆኑ በዚህ ሰዓት በአራስ ቤት 7 እናቶችና ከ7 ህፃናት ልጆቻቸው ጋር ይገኛሉ።

  • ራስ በማስቻል ሥራ 8 የሚያህሉ ወደ ማቋቋም የገቡ ሲሆን ሆፕ ፎር ኮራህ እና ላይፍ ጌት ተብለው ከሚጠሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በአብሮነት ሥራ ለማካሄድ እናቶችን ከነልጆቻቸውን ሊደግፋልን ስምምነት ላይ ደርሰናል ። ስለፈቃደኝነታቸውም በፋውንዴሽኑና በተጠቃሚዎች ሥም እናመሠግናለን።

  • በአራስ ቤት የሚገኙ ተጠቃማዎች በተቋሙ ውስጥ የቀለም ትምህርትና የተለያዩ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በተጨማሪም ከጥቅምት ጀምሮ ከማሠልጠኛና ከክፍለ ከተማው የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጋራ በመመካከር የቤት አያያዝን ሥልጠን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ነን።

  • የአልፋ ዐባል የሚሆኑ በየጊዜው እየጨመሩ ሲሆን የከፈሉበትን ደረሰኝ በመቁረጥ ሁሉ እንዲያውቀው ተደርጎል።

  • የአልፋ ዓመታዊ ልዩ ክብረ በዓል ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም ከ8:00-11:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌደሬሽን (ኢሰመኮ) ግቢ በደመቀ መልክ ተዘጋጅቷል። ስለዚህ ወዳጆች በዚህ ክብረ በዓል ላይ በክብር የተጋበዛችሁ በመሆኑ ከወዲሁ በማስታወሻ ላይ ቀኑን እንድታሳርፉ እየጠየቅን፣ ሌሎችን እሰከ ሁለት ሰው እንድትጋብዙ ለዚህም የጥሪ ወረቀት ከጽ/ቤቱ እንድትወስዱ በትህትና እንጠይቃለን።

  • የአልፋ ቦርድ፣ ግብረ ሀይሎችና ኮማቴዎች በተሰጣቸው ኀላፊነት የተገባቸውን ሥራ ለማከናወን እየተገናኙ ተመካክረዋል፣ አፈጻጸሙንም ተከታትለዋል።

በማጠቃለያ አልፋ በየጊዜው ስራው እንዲሰፉ፣ አስፈላጊው ሀብታት እንዲገኝ፣ ፍሬያማና ውጤታማ እንድንሆን ድጋፍ ስላደረጋችሁ ሁላችሁንም በድጋሚ እናመሠግናለን ። በቀጣዩም ሥራ አብረን እጅ ለእጅ በመያያዝ እንድንሠራ ጥሪ እናቀርባለን። ሥራዎቻችን ስለተሰሩልን፣ የአልፋ ቤተሰብን ስላገኘን አምላካችንን ከልብ እናመሠግናለን።

*** ልብታ፣ ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም ከ8:00-11:00 በኢትዮጵያና ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን(ኢሰማኮ) ግቢ የአልፋ የክብረ በዓል ቀን ስለሆነ በድጋሚ እንድትገኙ በማክበር ተጋብዘዋል።ቢያንስ አንድ ተጨማሪ እንግዳ ይጋብዙ።

የአምላክ ልጆች ፋውንድሽን-መስከረም 30/2014

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *